Fana: At a Speed of Life!

አንድ የእስራኤል የፓርላማ አባል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ እስራኤል የምክር ቤት ስብሰባዎችን አገደች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) አንድ የእስራኤል ፓርላማ አባል በቫይረሱ መያዙን ተከትሎ እስራኤል በርካታ የምክር ቤት ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ አግዳለች።

የምክር ቤት አባላቱም አስገዳጅ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር እንዳይመጡ ስትል ጉባኤዎችንም ላልተወሰነ ጊዜ አራዝማለች።

ሳሚ አቡ ሻዴህ የተባሉ አንድ የፖርላማ አባል በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ ራሳቸውን አግልለው መቀመጣቸው ቢገለጽም ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር መገናኘታቸው ተነግሯል።

የፓርላማው አባል በተለያዩ ዝግጅቶች፣ ለቅሶዎች እንዲሁም ጉባኤዎች ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎም ከእርሳቸው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎችም ራሳቸውን በማግለል እንደሚመረመሩም ጥሪ አቅርበዋል ነው የተባለው።

አያይዘውም”ቫይረሱ በመካከላችን እያለ በዝምታ መቀጠል ቫይረሱን እንዲዛመት ያደርጋል” የሚል መልዕክታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.