Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የከተማ ግብርና የመንግስት ትኩረት ሆኖ እየተሰራበት ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የከተማ ግብርና የመንግስት ትኩረት ሆኖ እየተሰራበት መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የክልሉ ከተሞች የመስኖ ስንዴ እርሻ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ነው ብለዋል።

ለአብነትም በሸገር ከተማ ብቻ 60 ሺህ ሄክታር በመስኖ ስንዴ በመሸፈን 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

መሰል ተሳትፎም ከተሞችን ከጠባቂነት ወደ አምራችነት ያሸጋግራል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

በሌላ በኩል ከተሞች ካላቸው ውስን መሬት ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ሲሉ አዳዲስ እውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ስለሚያላምዱ ለግብርናው ዘርፍ ሽግግር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting/
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.