Fana: At a Speed of Life!

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ 753 ቶን የዓሣ ምርት ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ 753 ቶን የዓሣ ምርት መገኘቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ ኢቴቻ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ምርቱ የተገኘው ባለፉት ሰባት ወራት ፈቃድ የወሰዱ አራት ዓሣ አምራች ማኅበራት በህዳሴው ግብ ሠው ሠራሽ ሐይቅ እንዲሰማሩ በማድረግ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ለ38 ማኅበራት በዘርፉ እንዲሰማሩ ፈቃድ መሰጠቱን ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ማኅበራቱ የገበያ ትስስር ችግር እንዳያጋጥማቸው ቀደም ብሎ የዝግጅት ሥራ መከናወኑንም አመላክተዋል፡፡

በሰለሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.