Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የጀግኖች ቅድመ አያቶቻችንን ገድል የዘከረ ነው – ኮሚሽነር መስፍን (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከ128 ዓመታት በኋላ የጀግኖች ቅድመ አያቶቻችንን ገድል የዘከረ ነው ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል::

ዋና ኮሚሽነር መስፍን (ፕ/ር) ከጉብኝቱ በኋላ÷ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከ128 ዓመታት በኋላ የጀግኖች ቅድመ አያቶቻችንን ገድል የዘከረ፣ ያለውን እና መጪውን ትውልድ ስለ ኢትዮጵያ እና የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተጋድሎ ቋሚ የታሪክ ሐውልት በመሆኑ ደስታዬ ወደር የለውም ብለዋል፡፡

ይህን ያሰቡና የሠሩም ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

የዓድዋ ድል ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በኅብረት ስለ ሀገር ፍቅር ተግዳሮቶችን በመቋቋም የድርሻውን አስተዋጽኦ ማበርከት የቻሉበት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ የታሪክ ማስታወሻዎችን በሚገባ አካትቶ የያዘ፣ ግዙፍ እና ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም አፍሪካውያንን የማሰባሰብ አቅም ያለው የዘመናችን የአንድነት ምልክት ሆኖ መገንባቱን አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.