Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የልማት ግቦች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ኩዋኩዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
አቶ አህመድ ሺዴ÷ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሒደት፣ በመልሶ ግንባታና የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
 
ቪክቶሪያ ኩዋኩዋ በበኩላቸው÷ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት ግቦች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
 
በተጨማሪም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ውስጥ ያሉ ትላልቅ የለውጥ እቅዶችን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደመከሩ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.