Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው የሕዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትን ለማሻሻልና ተደራሽ ለማድረግ የግል ባለሃብቱ ወደ ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲቀላቀል እድል መፈጠሩን አስታውሷል፡፡

በዚህ መሰረትም ዛሬ 20 አዳዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒባስ ታክሲዎች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡

ታክሲዎቹ በነበረው የስምሪት መስመርና ታሪፍ ከቦሌ-በሚሊኒየም-በስቴድዮም-ሜክሲኮ (ቡናና ሻይ ) እና ከቦሌ-በሚሊኒየም-በጊዮን_ፒያሳ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተጠቅሷል፡፡

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን በዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች መሰጠቱ የሕዝብ ትራንስፖርት አቅርቦቱን እንደሚያሻሽል የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የበካይ ጋዝ ልቀት በመቀነስና ከተማዋን የሚመጥንና ውብ ገፅታ ከመገንባት አንፃር የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.