Fana: At a Speed of Life!

26 ሺህ የኢንስታግራምና 34 ሺህ የቲክቶክ ተከታዮች ያሉት በጎ ፍቃደኛው ጥንቸል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 26 ሺህ የኢንስታግራም እና 34 ሺህ የቲክቶክ ተከታዮች ያሉት በሆስፒታል ለሚገኙ ህሙማን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጠው አሌክ የተሰኘ ጥንቸል በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን እያገኘ መጥቷል።

በጎ ፈቃድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን ለማገልገል በራስ ተነሳሽነት የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡

ይህም ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለመንግስት፣ ለእንስሳት፣ ለአካባቢ ሰፊ ጥቅም በመስጠት አንድም ሌሎችን ለማገዝ ወዲህም ለአዕምሮ እርካታ በሚል በጎ ፈቃደኞች አገልግሎታቸውን በገንዘብ ሣይተምኑ ይሰጣሉ፡፡

ስራውም በብዛት በሰው ልጆች የሚተገበር ነው፡፡ ፎክስ ኒውስ በዘገባው ያስነበበው ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

አሌክስ ይባላል፡፡ ጥንቸል ነው፡፡ በፈረንጆቹ 2020 ለምግብነት ሊውል የተገዛ ቢሆንም፥ ከምግብነት ባሻገር ለሰዎች ሕመም እፎይታን ይሰጣል ብሎ ያሰበ የለም፡፡

ጆሽ ሮው እና ኬይ ካቶ የተባሉ ጥንዶች ግን ራሩለት፤ ለእርድ ዝግጁ ከሚደረግበት ስፍራም ታደጉት፡፡ ቤተኛ ሆነ፡፡ ቤታቸውን ማድመቅ ብቻ ሣይሆን ሕመምን የሚያስረሳ በየሄዱበት የሚያስከትሉት ቤተሰብ አደረጉት፡፡

አሌክስ አሁን ላይ ባለቤቶቹን ብቻ ሣይሆን በሆስፒታል ውስጥ በበጎ ፈቃድ ያገለግላል፡፡ ሕመም ለተጫናቸው፣ ስቃይ ላደከማቸው፣ ሀዘን ላጠላባቸው ደስታን ይፈጥራል፤ የብዙዎችንም ቀልብ ገዝቷልም ነው የተባለው፡፡

በዚህም በሆስፒታል ብቻ ሣይሆን በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት ሰዎችን በማዝናናት ስራው ስሙ ናኝቷል፡፡

ጥንቸሉ አሌክስ ያለውን አነስ ያለ የኤሌክትሪክ መኪና አጠቃቀም በፍጥነት የተማረ ነው ብለዋል ባለቤቶቹ፡፡

በዚህም ዝናው አሌክስ ከ26 ሺህ በላይ የኢንስታግራም እና 34 ሺህ የሚሆን የቲክቶክ ተከታዮችን አፍርቷል መባሉም አጃኢብ አስብሏል ብዙዎችን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.