Fana: At a Speed of Life!

የተከዜ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአራት ዓመታት ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የቆው የተከዜ ወንዝ ድልድይ ከ256 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው መጀመሩ ተገለጸ፡፡

ግንባታው በሦስት ወራት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ መገለጹን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመት ከ155 ሜትር በላይ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ በመካከል ከ60 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ተገጣጣሚ የብረት ድልድይን መሠረት አድርጎ እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው ተብሏል፡፡

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን የዝቋላ እና ሰሀላ-ሰየምት ወረዳዎች መካከል የሚገኘው ድልድይ÷ ብሔረሰብ አስተዳደሩን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጋር የሚያገናኝ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቀደም ሲል የነበረው ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ በደለል በመዋጡና በጎርፍ በመወሰዱ ምክንያት ላለፉት 4 ዓመታት አገልግሎት ሳይሰጥ መቆየቱም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.