Fana: At a Speed of Life!

ቶማስ ቱኸል በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሙኒክ ጋር ይለያያሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከባየርን ሙኒክ ጋር እንዲለያዩ መወሰኑን ክለቡ አስታወቀ፡፡

አሰልጣኙ አንድ ዓመት የኮንትራት ጊዜ ቢኖራቸውም የክለቡ አመራሮች በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከመከሩ በኋላ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ እንዲለቁ ወስነዋል፡፡

ውሳኔው የተላለፈውም ባየርንሙኒክ ከ12 ዓመታት በኋላ ባጋጠው ተደጋጋሚ ሽንፈት ምክንያት ከዲ ኤፍ ቢ ፖካል ዋንጫ ውጪ መሆኑን እና ከቡንደስ ሊጋው ፉክክርም ከመሪው በ8 ነጥብ ልዩነት ተበልጦ መቀመጡን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የ50 ዓመቱ ቶማስ ቱኸል በ2023 መጋቢት ወር ላይ ጁሊያን ኔግለስማንን በመተካት ባየርንሙኒክን መረከባቸው ይታወሳል፡፡

ሙኒክን ከመረከባቸው ቀደም ብሎም የቼልሲ እና የቦርሺያ ዶርትሙንድ አሰልጣኝ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.