Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት የሥራ ዕድል ለመፍጠር የመዳረሻ ሀገራትን የማስፋት ሥራ መጠናከሩን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ሀገራት ምቹ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የመዳረሻ ሀገራትን የማስፋት ጥረታችንን አጠናክረን ቀጥለናል ሲሉ የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከኳታር የሥራ ሚኒስትር አሊ ቢን ሳሚክ አል ማሪ (ዶ/ር) ጋር በዶሃ ተወያይተዋል፡፡

የሥራ ዲፕሎማሲው የሥራ ዕድልን ከማስፋት ባሻገር የሀገራቱን ግንኙነት በይበልጥ እንደሚጠናክር ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል ከነበረው የቤት ውስጥ ሥራ ስምሪት ባሻገር በአዲስ መልክ የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ለኳታር የሥራ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱንም አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.