Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ 13ኛውን የማዕቀብ ማዕቀፍ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ 13ኛውን የማዕቀብ ማዕቀፍ ማፅደቁ ተሰማ፡፡

የአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች በሩሲያና በዩክሬን መካከል ካለው ሁኔታ በመነሳት በሩሲያ 13ኛው የማዕቀብ ማዕቀፍ ላይ በመርህ ደረጃ መስማማታቸው ተጠቁሟል፡፡

ማዕቀፉ በአውሮፓ ህብረት ከፀደቁት ማዕቀቦች አንዱና ሰፊው እንደሆነና ፅሑፋዊ አሰራርን በመከተል በመደበኛነት በፈረንጆቹ የካቲት 24 እንደሚፀድቅ በቀረበው መግለጫ ተመላክቷል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በ27 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የተደረሰውን ስምምነት በደስታ እንደተቀበሉና ማዕቀቡም የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የመጠቀም እድልን እንደሚቀንስ ተናግረዋል።

ዲፕሎማቶች እንደተናገሩት የአውሮፓ ህብረት አዲሱ ማዕቀብ የሰሜን ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ካንግ ሱን ናም ለሞስኮ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ከማቅረብ ጋር ተያይዞ የንብረት እና የቪዛ እገዳ ይጥላል።

የአውሮፓ ኅብረት በሁለቱ ዓመታት ጦርነት ውስጥ ሩሲያ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ማዕቀብ የጣለ ሲሆን እስካሁን 2 ሺህ የሚሆኑ ባለሥልጣናት እና ንብረቶችን በጥቁር መዝገብ ማስፈሩንም ሲጂቲኤን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.