Fana: At a Speed of Life!

የ2ኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብርና የውድድር ሜዳዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሐ-ግብርና የመጫዎቻ ሜዳዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛው ዙር ውድድር በድሬደዋ ስታዲየም የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀምር መገለፁ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም እና ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት የሚካሄዱ ጨዋታዎች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄዱ ተመላክቷል፡፡

የመጨረሻዎች ሦስት ሳምንታት ጨዋታዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡

መርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያሉበትን ጨዋታዎች እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታዎችን ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.