Fana: At a Speed of Life!

አቶ አወል አርባ በክልሉ የተጀመረው የዘር ብዜት ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመረው የዘር ብዜት ሥራ ተስፋ ሰጭ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ አሳሰቡ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዱብቲ ወረዳ እየተከናወነ የሚገኘውን የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት የሥራ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ አወል በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ የክልሉ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም እያከናወነ የሚገኘው የምርጥ ዘር ብዜት ተስፊ ሰጪና የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

የዘር ብዜት ሥራው ክልሉ ያለውን ሰፊ ለም መሬት፣ የውኃ አማራጮችና የሰው ሃብት አቀናጅቶ በምግብ እራስን ለመቻል የሚደረጉ ጥረቶችን በዘላቂነት የሚፈታ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የተጀመሩ ሥራዎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰባቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

በክልሉ በግብርና መስክ የተሰማሩ ባለሃብቶች፣ የምርምር ተቋማትና ኢንተርፕራይዞችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትም የበኩላቸውን ገምቢ ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.