Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአመራር ምዘና እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈፃፀሞችን መሰረት በማድረግ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የአመራር ምዘና እየተካሄደ ነው።

በፓርቲው የክልሉ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጃት ዘርፍ ሀላፊ ይግለጡ አብዛ እንዳሉት÷ ምዘናው የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈጻጸሞችን መሰረት በማድረግ ተከናውኗል፡፡

ውጤትን መሰረት ባደረገ፣ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ ወጥና ፍትሓዊ በሆነ መንገድ ምዘናዉን በማስፈጸም የፓርቲውን አመራር ጥራትና ውጤታማነት ማሳደግ የምዘናው ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል።

የአመራር ምዘናው የአመራሩን ጥንካሬ በማጎልበት፣ ውስንነቶችን በማረም እና ጠንካራ የአመራር ስርዓት እውን በማድረግ የተጠናከረ ፓርቲና መንግስት ለመገንባት መሰረት እንደሚሆን መነገሩን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መድረኩ የክልሉ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትም ከየተልዕኳቸው አንጻር የ2016 በጀት ዓመትን ያለፉት ስድስት ወራት የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈጻጸሞችን መሰረት አድርገው ራሳቸውን የሚፈትሹበት ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.