Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የዲፕሎማሲ ስኬት የተገኘበት ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ የዲፕሎማሲ ስኬት የተገኘበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ መደበኛ መግለጫ ተሰጥቷል፡:

መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር)÷ የአፍሪካ ህብረት ጉባዔን ጨምሮ በሳምንቱ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብሩ መልከ-ብዙ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት ጉባዔን ለመታደም ለመጡ መሪዎች በሚኒስትሮች ደረጃ አቀባበል የተደረገበትና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት እና የአለም የዲፕሎማቲክ መናኸሪያነቷን ያረጋገጠችበት መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም የዲፕሎማሲ ስኬት የተገኘበት መሆኑን አንስተው፤ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የነበሩ ስምምነቶችን የመፈተሽና አዳዲስ የትብብር ስምምነቶች የተከናወኑበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ከ7 አመታት በኋላ በተካሄደው የኢትዮጵያ እና ኬንያ የሚኒስትሮች ጉባዔም የሁለቱን ሀገራት ትብብርና አብሮ መስራት የሚያጠናክሩ ስምምነቶች መደረጋቸውን ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.