Fana: At a Speed of Life!

የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ በባለሃብቶች መያዙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ 19 የማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ በባለሃብቶች መያዛቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚአቶ አክሊሉ ታደ በኢትዮጵያ ከተመድ ዋና ተወካይ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) ጋር በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያሉ አምራች ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው በጉብኝቱ ወቅት÷ በፓርኩ ያሉ 19 የማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ በውጪና በሀገር ውስጥ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ተይዘው ከ7 ሺህ በላይ የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል።

አሁን ላይም በኢንቨስትመንት መሰማራት ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሃብቶች ፓርኩ ሁለት ሄክታር የሚጠጋ የለማ መሬት ዝግጁ እንዳደረገ መናገራቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለዚህ ውጤት መሳካት ኮርፖሬሽኑ ባለፈው አንድ ዓምት የአምራች ዘርፍ ብዝሃነት ላይ እንዲሁም ለአምራቾች ተጨማሪ የገበያ አማራጮችን ማግኘት ላይ ያከናወናቸው የማሻሻያ ተግባራት ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.