Fana: At a Speed of Life!

ከቅባትና ጥራጥሬ እህሎች የወጪ ንግድ ከ285 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከቅባትና ጥራጥሬ እህሎች የወጪ ንግድ 285 ነጥብ 53 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በ2016 ዓ/ም የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከቅባት እህሎች የወጪንግድ 109 ነጥብ 66ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን አፈጻጸሙም 109 ነጥብ 40 በመቶ መሆኑን ሚኒሰቴሩ በስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ይህም ካምናው ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ25 ነጥብ 94 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

በስድስት ወራቱ በጥራጥሬ እህል የተገኘው ገቢ 175 ነጥብ 87 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን በመቶኛ ሲሰላ 131 ነጥብ 89 በመቶ ነው ተብሏል፡፡

ካለፈው ተመሳሳይ ወቅተ ጋር ሲነጻጸርም የ76 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከቅባትና ጥራጥሬ እህሎች የወጪ ንግድ በድምሩ 285 ነጥብ 53 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የሰሊጥ እህል ላይ አለም አቀፍ የገበያ ፍላጎት መጨምሩ ፣ የጉሎ ፍሬ ለአለማቀፍ ገበያ ምርት በበቂ መቅረቡ ፣ላኪ ድርጅቶች በወቅቱ ወደ ውጭ መላክ የሚችሉበት የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ መደረጉ ከወጪ ግብይት የተገኘው ገቢ እንዲሻሻል ያደረጉ ምክንያቶች ናቸውም ተብሏል፡፡

ከቅባት እህሎች መዳረሻ ሀገራት መካከል እስራኤል፣የተባበሩት አረብ ፣ሲንጋፖር፣ቪትናም እና አሜሪካ በቀዳሚነት ሲጠቀሱ ህንድ ፣ፓኪስታን፣ሲንጋፖር፣ቪትናም እና ኬንያ ደግሞ ከጥራጥሬ አህል መዳረሻዎች መካከል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በእቅድ አፈጻጸሙ ካጋጠሙ ተግዳሮቶች መካከልም የፀጥታ ችግር ፣የሎጀስቲክ ወጪ መጨመር ፣የኮንትሮባንድ መስፋፋት ፣ የግብይት ህጎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ተግባራዊ አለማድረግና የአቅም ዉስንነት ተጠቅሷል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.