Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጆርዳን በቱሪዝም መስክ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጆርዳን በቱሪዝም መስክ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።

የጆርዳን የቱሪዝም፣ የሃይማኖት እና የትምህርት ሴሚናር በሀገሪቱ ኤምባሲ አዘጋጅነት ተካሂዷል።

በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ፥ ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ኢትዮጵያና ጆርዳን በቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በቱሪዝም ኢንቨስትመንት፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ጥቅሎችን በማዘጋጀት እና በአቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት ከጆርዳን ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷልም ነው ያሉት።

የጆርዳን የቱሪዝም ሚኒስትር መክራም ሙስጠፋ በበኩላቸው እንዳሉት ፥ ጆርዳንና ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።

ይህንን አጋርነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የቱሪዝም ዘርፍ አንዱ መሆኑን ገልጸው ፥ በዘርፉ በተለያዩ መስኮች ትብብርን ለማጠናከርና በጋራ ለመሥራት ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የጆርዳን የቱሪዝም ሚኒስትር እና ልኡካቸው ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.