Fana: At a Speed of Life!

36ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 36ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የውይይት መድረኩ “የዓድዋ ድል ለወል ትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሃይሉ አዱኛ እንዳሉት÷ ዓድዋ ኢትዮጵያውያን ለነፃነታቸው የተዋደቁበት እና በአንድነት የተሰለፉበት ድል ነው፡፡

የአሁኑ ትውልድም አባቶች ደምና አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡትን ነጻ ሀገር ማስቀጠል አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በመድረኩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎቸ እና የታሪክ ምሁራንን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.