Fana: At a Speed of Life!

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመላ ሀገሪቱ ከተውጣጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና አመራሮች ጋር እየተወያየ ነው።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት አለባቸው ብለዋል፡፡

በእስካሁኑ ሒደትም ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሚዲያ ተቋማትና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር የተለያዩ የውይይት መድረኮች መካሄዳቸውን አንስተዋል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በእውቀታቸውና በመሳሰሉ ተግባራት በምክክር ሒደቱ ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ጽንሰ ሃሳብና ስለ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስፈላጊነት ለተሳታፉዎቹ ገለጻ ተደርጓል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ እና ሰለሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.