Fana: At a Speed of Life!

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከጣልያን በልጧል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ መድረሱ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም በሃገሪቱ በኮቪድ19 ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከአውሮፓዊቷ ጣሊያን መብለጡ ነው የተነገረው።

እስካሁን ባለው ሂደትም ከአሜሪካ እና ብሪታንያ ቀጥሎ በርካታ ሰዎች በኮቪድ19 ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉባት ሃገር ሆናለች።

ከዚህ ባለፈም በሃገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 580 ሺህ ደርሷል ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንት ቦልሶናሮ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ይሰጡት የነበረውን አስተያየትና ሃሳብ ማቆማቸውም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.