Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዓለም አቀፉ የ9ኛ ኢስላሚክ ሪቴል ባንኪንግ ተሸላሚ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳውዲአረቢያ ሪያድ በተካሄደ የሽልማት ስነ-ሥርዓት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፈረንጆቹ 2023 በሪቴል ኢስላሚክ ባንኪንግ በኢትዮጵያ ተስፋ የሚጣልበት ባንክ በመባል ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
 
ሽልማቱን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በስፍራው በመገኘት ተቀብለዋል፡፡
 
ም/ፕሬዚዳንቱ ከሽልማቱ በኋላ እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዚህ ሽልማት የበቃው በሲቢኢ ኑር የባንክ አገልግሎት ባለፉት ዓመታት በፋይናንስ አፈፃፀም የኢስላሚክ ባንኪንግ አገልግሎትን ሳይሸራረፍ ተግባራዊ በማድረግ ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ነው፡፡
 
ሽልማቱ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት ባንኩ እያከበረ ባለበት ወቅት የተበረከተለት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡
 
የተገኘው ውጤት ከባንኩ ጋር የሚሰሩ መላው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች፣ የባንኩ ሠራተኞች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦርድ አመራሮችና የሸሪዓ አማካሪዎች ድምር የስራ ውጤት መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡
 
አገልግሎቱን ከዚህ የበለጠ ለማሳደግ የሁሉም ወገን የጋራ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ባለፉት 10 ዓመታት ላስመዘገበው ውጤት መሸለሙ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
 
የሲቢኢ ኑር የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን አስተዋፅኦ ለማጠናከርና እስካሁን የተፈጠረውን ግንዛቤ ወደ ተጨባጭ ለውጦች ለማሸጋገር ባንኩ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፈው ዓመት ጅቡቲ በተካሄደው 12ኛ ዓለም ዓቀፍ የኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት በዘርፉ ኢትዮጵያ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ሽልማት መቀበላቸው ይታወሳል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.