Fana: At a Speed of Life!

አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም ተገላገለች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በስልጤ ወረዳ አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም መገላገሏ ተሰማ።

የወረዳው ሰነና ገሬራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ዜኖ ሸምሱ በቅበት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላት የቀዶ ህክምና 3 ሴት እና 1 ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።

በአሁኑ ሰዓት ህፃናቱ በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

በአካባቢው 4 መንትዮችን መገላገል እምብዛም የተለመደ እንዳልነበር ተገልጿል።

የ30 ዓመቷ ወይዘሮ ዜኖ ከዚህ ቀደም 4 ልጆችን በሰላም የተገላገለች ሲሆን የቅድመ እና የድህረ ወሊድ ክትትል ስታደርግ እንደነበር ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.