Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ወጣት አመራሮች ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር በጋራ ያዘጋጁት የአፍሪካ ወጣት አመራሮች ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በመድረኩ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ከ200 በላይ ወጣት አመራሮች ታድመዋል::

ወጣቶቹ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በአመራርነት፤ ዲፕሎማሲና በዓለም አቀፋዊ ግንኙነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ መርሃ-ግብር እንደሚያካሄዱ ተገልጿል::

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የነገዋ አፍሪካ እድል ፈንታ የሚወሰነው አሁን ላይ ባሉ ወጣቶች ነው ብለዋል።

በመሆኑም የአፍሪካ ወጣቶች በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ በጋራ የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት ሊሰሩ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የወጣቶችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ በማረጋገጥ የምንመኛትን አፍሪካ እውን ለማድረግ መስራት ይገባል ብለዋል::

በተለይም በአመራርነት ላይ ያሉ ወጣቶችን በማበረታታትና ተሳትፎአቸውን በማሳደግ አህጉሪቷን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማህበር ዋና ዳይሬክተር ጫላ አሰፋ (ኢ/ር) የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን ወጣቱ ትውልድ አቅሙን መጠቀም እንደሚገባው ጠቅሰው፤ ለዚህም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ መስክ ለጋራ ስኬት ሊሰራ ይገባል ብለዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.