Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን የሚመጥን የሜካናይዝድ ኃይል እየተገነባ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የሚመጥን የሜካናይዝድ ኃይል እየተገነባ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።

የሜካናይዝድን የግዳጅ አፈፃፀም ብቃት ለማሳደግ በተዘጋጀ ጥናት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ጀነራል መኮንኖችና ከሁሉም የሜካናይዝድ ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች በተገኙበት በአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የሜካናይዝድ ኃይሉ ራሱን ችሎና ከእግረኛ ሰራዊት ጋር በመሆን በርካታ ግዳጆችን መፈፀሙን አንስተዋል።

በቀጣይ ሊኖር ከሚችል ግዳጅና ነገን ታሳቢ ያደረገ ሜካናይዝድ እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች እንደተቋም የተዘጋጀው ጥናት ለቀጣይ ግዳጅ አፈፃፀም የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን መናገራቸውን ማንሳታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡።

የተዘጋጀውን ጥናታዊ ፅሑፍ የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ይታያል ገላው ያቀረቡ ሲሆን በጥናቱ መሠረት በሰው ኃይል ሜካናይዝድ ክፍሎቹ ላይ የሚኖረውን አወቃቀር በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.