Fana: At a Speed of Life!

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 447 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት፣የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) ፣ የተመራቂ ወላጆች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፤

ለ11ኛ ዙር ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው ተቋሙ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር 2 ሺህ 306፣ በሁለተኛ ድግሪ 141 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡

ከዕለቱ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 43ቱ የሕክምና ዶክተሮች ፣ 271 በዲፕሎማ መርሀ ግብር በመምህርነት ሙያ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው 2 ሺህ 447 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ሚኒስትር ዴዔታ እና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ብርሃኑ ሌንጂሶ(ዶ/ር) ÷ኢትዮጵያ ብዝሃ ባሕል፣ ዕምነትና የተትረፈረፈ ሀብት ቢኖራትም በብቁ የሰው ኃይል ዕጥረት ሳቢያ ስትፈተን ቆይታለች ብለዋል።

በቴክኖሎጂ ዘመን መመረቃችሁ ዕድለኛ ያደርጋችኋል ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው እንደሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች በዕውቀት ለመፍታት እና በጎ ሚናችሁን ለማኖር ቁልፉ በእጃችሁ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ለሀገራችሁ የመፍትሄ አካል መሆን ይኖባችኋል፤ በቀጣይም ለአዲስ ልምምድና የመፍትሄ ሃሳብ ራሳችሁን በዕውቀት ልታበለፅጉ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሐብታሙ አበበ(ዶ/ር) በበኩላቸው፥   ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በማሕበረሰብ አገልግሎት እና በምርምርና ስርፀት በተመረጡ መስኮች ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል።

 

 

 

 

 

 

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.