Fana: At a Speed of Life!

አቶ  ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፉ የጥቁር ሕዝቦች የታሪክ፣ የቅርስና የትምህርት ማዕከል የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የታሪክ፣ የቅርስና የትምህርት ማዕከል የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና ሮቢ ዋከርን የማዕከሉ የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

አቶ ጸጋዬ ጨማን ደግሞ የማዕከሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ መርጧል።

ማዕከሉ ዛሬ የቀጣይ የተቋሙ መተዳደሪያ ደንብን ይፋ ያደረገ ሲሆን÷ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ጠቅላላ ጉባኤውምን አካሂዷል።

በዚህም ማዕከሉ የዓለም አቀፍ ጥቁሮች ንቅናቄ ማህበር መስራች በመባል የሚታወቁትን ማርከስ ጋርቬ ልጅ፣ ጁሊየስ ጋርቬን (ዶ/ር) ደግሞ የበላይ ጠባቂ አድርጎ መርጧል።

ማዕከሉ የጥቁር ህዝቦችን ታሪክ ቅርስ እና ትምህርት መሰረት ያደረገ ስራ የሚያከናውን ሲሆን÷ ደረጃውን የጠበቀ የምርምር ማዕከልን የማቋቋም እና የተሻለ የትምህርት ስርዓት በመፍጠር በራሱ መተማመ የሚችል ወጣት እንዲፈጠር የሚሰራ ይሆናል ተብሏል።

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.