Fana: At a Speed of Life!

የጀመርናቸውን ስራዎች እያላቅን የመረጠንን ህዝብ ማገልገላችንን እንቀጥላለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀመርናቸውን ስራዎች እያላቅን የመረጠንን ህዝብ በታማኝነት እና በትጋት ማገልገላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ የ3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤያችንን በማካሄድ የግማሽ ዓመት አፈጻጸማችንን የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ ለሆነው የከተማችን ምክር ቤት አቅርበናል ብለዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የከተማዋን ሰላማዊ ሁኔታ በማረጋገጥ የህዝቡን ተጠቃሚነት በማላቅ በርካታ የልማት ስራዎችንና የነዋሪዎቻችን የኑሮ ሸክም ያቃለሉ ሰው ተኮር ተግባራትን ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል።

የከተማችንን ገፅታ የቀየሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለህዝብ አገልግሎት ያበቃንበት ወቅት መሆኑን ምክር ቤቱ አረጋግጧል ሲሉም ጠቅሰዋል።

ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ በማድረግ፣ የህዝብ ተሳትፎን ይበልጥ በማጎልበት፣ ሰላማዊ ሁኔታውን በማስቀጠል፣ የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉና አገልግሎትን የሚያሻሽሉ ስራዎችን እንተገብራለን ብለዋል።

በዚህም መዲኛችን ፅዱና ውብ እንድትሆን የጀመርናቸውን ስራዎች እያላቅን የመረጠንን ህዝብ በታማኝነት እና በትጋት ማገልገላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.