Fana: At a Speed of Life!

በወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

6ኛው የአፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር በቱኒዚያ ሃማማት መካሄድ ጀምሯል፡፡

ዛሬ በተካሄደው የወጣት ሴት 6 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርም÷ ሮቤ ዳዲ 1ኛ፣ የኔነሽ ሽመክት 2ኛ እንዲሁም ትነበብ አስረስ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በዚሁ ርቅት መቅደስ ዓለምእሸት 4ኛ፣ ኮኮቤ አበራ 5ኛ እና አልማዝ ዮሐንስ 8ኛ ደረጃ መያዛቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በ6ኛው የአፍሪካ የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና አዋቂ ሴት 10 ኪሎ ሜትር ውድድር÷ ደጊቱ አዝመራ 3ኛ፣ አንቺንአሉ ደሴ 5ኛ፣ ጽጌ ኃይለሥላሴ 8ኛ፣ ያልጋ ሰውአገኝ 9ኛ፣ ፋንታዬ በላይነህ 11ኛ እና ዘበናይ አያና 12ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.