Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 176 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 176 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 1 ሺህ 282 አዳዲስ ባለሃብቶች ወደ ስራ መግባታቸውን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀጸም ግምገማ እያካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ÷ ክልሉ በጸጥታ ችግር ውስጥ ሆኖም በኢንቨስትመንት መስክ አበረታች ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በስድስት ወራት ውስጥ በክልሉ 176 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 1 ሺህ 282 አዳዲስ ባለሃብቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው÷ በዚህም 226 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

19 የሚደርሱ ኢንዱስትሪዎች እና ስድስት በአበባ ልማት የተሰማሩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ከ35 ሚሊየን በላይ ዶላር ገቢ ማስገኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡

89 የሚደርሱ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከውጭ የሚገባን ተኪ ምርት በማምረት ወጪ ሊደረግ የነበረ 41 ሚሊየን ብር ማዳን መቻሉ ተገልጿል፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.