Fana: At a Speed of Life!

በህንድ አንድ የጭነት ባቡር 70 ኪሎ ሜትር ያለ ካፒቴን መጓዙ እያነጋገረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ አንድ ጠጠር የጫነ ባቡር 70 ኪሎ ሜትር ያለምንም ካፒቴን መጓዙ መገናኛ ብዙሃንን እያነጋገረ ይገኛል፡፡

ባቡሩ ከሰሜናዊ ጃሙ ግዛት በመነሳትወደ ፑንጃብ እና ካሽሚር ሲንቀሳቀስ እንደነበር የተገፀ ሲሆን 70 ኪሎ ሜትር ያለ ካፒቴን መጓዙ ተገልጿል፡፡

ድርጊቱ የተከሰተው ባቡሩ በጃምሙ የባቡር ጣቢያ ላይ ተረኛ ሰራተኞችን ለመቀየር ከቆመ በኋላ በተፈጠረ አለመግባባት ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

የሰሜን ባቡር መስመር ቃል አቀባይ ዴፓክ ኩመር÷ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንገደኞችን በሚያጓጉዘው የህንድ የባቡር አውታር ላይ የደረሰው ይህ ክስተት አደጋ አለማድረሱን ተናግረዋል።

ባቡሩ ያለ ካፒቴን እንዲጓዝ የተደረገበት ጉዳይ እየተጣራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በባቡር አደጋ ምክንያት በርካታ የሰውና የንብረት ጉዳት እያጋጠማት የምትገኘው ህንድ የባቡር መስመሮቿን እና ጣቢያዎቿን ለማዘመን ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቷን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.