Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ኢትዮጵያ ሳምንት መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የዲጂታል ኢትዮጵያ ሳምንት “የጋራ ጥረታችን ለዲጂታል ኢትዮጵያችን” በሚል መሪ ሐሳብ መካሄድ ጀመረ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቀት ባደረጉት ንግግር፥ ከ526 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ አግባብ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የአጋማሽ ዘመን ጉዞና የኤሌክትሮኒክ መንግሥት ሥራዎች መቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ቀናትም የሣይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ፣ ወረዳኔት፣ ኢ-ኮሜርስ ስትራቴጂ፣ የግል ዳታ ጥበቃ፣ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት ስትራቴጂ፣ የመንግሥት የኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር፣ የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የብሔራዊ ዳታ ማዕከል፣ የዳታ አሥተዳደርን ጨምሮ በሌሎች ቁልፍ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ሳምንቱ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎችን ለማስተዋወቅና ማኅበረሰቡ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀም ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.