Fana: At a Speed of Life!

የኤቨርተን ቅጣት ወደ 6 ነጥብ ዝቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሦስት ወራት በፊት 10 ነጥብ ተቀንሶበት የነበረው ኤቨርተን ቅጣቱ ወደ 6 ነጥብ ዝቅ ተደርጎለታል፡፡

ኢቨርተን ነጥቡ ከመቀነሱ በፊት በሊጉ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን ከቅጣቱ በኋላ ወደ 19ኛ ደረጃ እንደወረደና ይህም በቡድኑ ውስጥ ድንጋጤ መፍጠሩ አይዘነጋም፡፡

በወቅቱ በተላለፈው ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ የነበረው ኤቨርተን ቅሬታ እንደሚያቀርብ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ቡድኑ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ቅጣቱ ወደ 6 የፕሪሚየር ሊግ ነጥብ ዝቅ እንዲል መወሰኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የቅጣት ውሳኔው መሻሻል ኤቨርተንን ከ17ኛ ወደ 15ኛ ደረጃ ከፍ ያደረገው ሲሆን በሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በሚገኙት በርንሌይ እና ሼፊልድ ዩናይትድ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚያሰድር ተነግሯል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.