Fana: At a Speed of Life!

እስራኤልና ሃማስ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ የ40 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጦርነት ውስጥ የሚገኙት እስራኤል እና ሃማስ በመጪው የረመዳን ወር የተኩሰ አቁም ለማድረግ መቃረባቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ፡፡

ባይደን ስለ ወቅታዊው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት አስመለክተው እንደተናገሩት÷ ሃማስ ከረመዳን ወር አስቀድሞ የ40 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የቀረበውን ረቂቅ ሰነድ እያጤነው ይገኛል፡፡

በቀረበው ረቂቅ ሰነድ መሰረት ሃማስ የእስራኤል ታጋቾችን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ከሆነ በመጪው ሰኞ ጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን እና ሃማስ በሰነዱ እንደሚስማማ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የብሄራዊ ደህንነት አማካሪዬ እንደነገረኝ ሁለቱ ወገኖች ተኩስ አቁም ለማድረግ ተቃርበዋል፣ ነገር ግን ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም ሁለቱ ወግኖች ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብዬ አስባለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲሆን ሃማስ 40 የእስራኤልን የጦር እስረኞችን የሚለቅ ሲሆን እስራኤልም በምላሹ ከ400 በላይ የፍልስጤም ታጋቾችን የምትለቅ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በስምምነቱ መሰረት እስራኤል የረመዳን ወር ከገባ በኋላ ምንም አይነት ዘመቻ አታደርግም የተባለ ሲሆን በሚኖረው የተኩስ አቁም በጋዛ ሰርጥ የወደሙ ሆስፒታሎች እንደሚገነቡ እና የሰብዓዊ እርዳታዎች እንደሚገቡ አርቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.