Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ የሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግ ላይ ተኩረት ተደርጎ ይሰራል- ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግ በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2016 ዓ.ም የስድስት ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷በቀጣይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እንዲሰራባቸው ከታቀዱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሠራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግ በቀዳሚነት ተጠቀምጧል፡፡

በተጨማሪም የጋራ የገቢ አቅምን የሚያሳድጉ ስራዎችን መተግበር፤ የአመራር አቅምን ማሳደግ፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ግንባታ የማስፈፀምና የማጠናቀቅ ፤ ፖሊሳዊ ሙያን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ የሚሉትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ኮሚሽነር ጄነራሉ አንስተዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ የሀገርን ሰላምና ደኅንነት በመጠበቅ እንዲሁም የፖሊስን ተቋም ለመቀየር ራሳቸውን መስዋዕት አድርገዋል ላሏቸው የፖሊስ አመራርና አባላትም ምስጋና ማቅረባቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ባለፉት ስድስት ወራት በቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽን፣ በሰው ኃይል ልማት፣ በሎጂስቲክስ አቅም ግንባታ፣ በመረጃ መር ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት እና በገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ስኬቶች መመዝገባቸው ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.