Fana: At a Speed of Life!

128ኛው የዓድዋ ድል በድምቀት ይከበራል – ጀኔራል አበባው ታደሰ  

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በድምቀት እንደሚከበር የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ ገለፁ።

የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችን ሪፖርት ያዳመጡት ጀኔራል አበባው÷ 128ኛው የዓድዋ ድል ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ወቅቱን በሚዘክር እና ክብሩን በሚመጥን መልኩእንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡

በዓሉን ለማክበር በወጣው ዕቅድ መሠረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችም የዓድዋ ጀግኖችን የሚዘክር የ34 ደቂቃ ዶክመንታሪ፣ ቢል ቦርድ፣ በራሪ ወረቀቶች፣ ሎጎ፣ መሪ ቃል እና ሠራዊቱ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የሚወያይበት ጽሑፍ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

የካቲት 23 ቀን ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒት እና ድሉን የሚያስታውሱ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.