Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዩ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት በቀጣይ ለሚካሄደው የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተገኝተው ቀጣዩን የሕዝብና ቤት ቆጠራ በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ቀጣዩ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሦስት ዓመቱ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም አካል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ለሕዝብና ቤት ቆጠራው የሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይም ምክክር ከተደረገ በኋላ÷ አቶ ተመስገን የሥራ መመሪያና አቅጣጫ መስጠታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.