Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኬንያ ግንኙነታቸውን በይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ ያላቸውን ጥልቅ እና ታሪካዊ ግንኙነት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት በሀገሪቱ በፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በስቴት ሀውስ ኬንያ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ሁለቱ መሪዎች እና ልዑካን ቡድኖቻቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ እያደረጓቸው ያሉ ጉልህ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ጅማሮ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁለቱ መሪዎች የሁለቱን ሀገራት ጥልቅ እና ታሪካዊ ግንኙነት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር አውስተው ይህንኑ በቁርጠኝነት ማጠናከር እንደሚገባ ተስማምተዋል።

ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወሳኝ አጋጣሚ ሆኖ የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የበለጠ ለማዳበር ብሩህ መፃዒ ጊዜን ያመላከተ ሆኗል መባሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.