Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከጀርመንና ከፈረንሳይ ጋር ያላት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያ ከጀርመን እና ከፈረንሳይ ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አበክሮ እንደሚሰራ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
 
ምክትል ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውር እና የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
 
በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ከጀርመን እና ከፈረንሳይ ጋር እንዳላት ያነሱት አቶ አደም፤ ይህ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ብልፅግና ፓርቲ አበክሮ ይሰራል ብለዋል።
 
በመርህ ላይ የተመሰረተ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ግቡ ያደረገ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረትን ዓላማ ያደረገው ብልጽግና ፓርቲ፤ በዚሁ መርህ ላይ ተመስርቶ ከጀርመን እና ፈረንሳይ ጋር ያለውን ወዳጅነትን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚንቀሳቀስ አብራርተዋል።
 
በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ግንኙነት የታጀበው ኢትዮጵያ ከሁለቱ ሀገራት ጋር የገነባችው ግንኙነት ወደ ተሻለ ትብብርና አጋርነት እንዲያድግ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላትም ገልፀዋል።
 
አምባሳደሮቹ በበኩላቸው በልማት፣ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲሁም በሽግግር ፍትህና በአካታች ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥረቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
 
አቶ አደም በውይይቱ ላይ በመንግስት እና በፓርቲ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በተለያዩ መስኮች የተገኙ ሀገራዊ ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የወዳጅ ሀገራት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ማንሳታቸውን ከፓርቲው ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.