Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የሰራችው 2ኛው ግዙፍ መርከብ በፈረንጆቹ 2026 ለአገልግሎት ይበቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና 2ኛው በሀገር ውስጥ የተገነባ ግዙፍ የመዝናኛ መርከብ በመገጣጠም ላይ ሲሆን በፈረንጆቹ 2026 መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ የሻንጋይ ዋይጋኦኪዮ መርከብ ግንባታ ኩባንያ አስታውቋል።
 
በፈረንጆቹ 2026 መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ከወደብ እንደሚነሳ፣ የሙከራ ጉዞውም በፈረንጆቹ ሰኔ 2026 እንደሚጀምር ኩባንያው ገልጿል።
 
የመርከቧ ስም እና አቅርቦትም ዓመቱ ከመገባደዱ በፊት እንደሚከናወንም አመላክቷል።
 
በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ውስጥ ከተሰራው ግዙፍ የመዝናኛ መርከብ “አዶራ ማጂክ ከተማ” ጋር ሲነፃፀርም አዲሱ መርከብ በርዝመት፣ በስፋት እና በክብደት እንደሚበልጥ ተገልጿል፡፡
 
መርከቡ በአጠቃላይ 142 ሺህ ቶን ክብደት፣ ርዝመቱ 341 ሜትር፣ ስፋቱ 37 ነጥብ 2 ሜትር እና 2 ሺህ 144 ክፍሎች ያሉት በመሆኑ ከመጀመሪያው መርከብ በክብደት፣ ርዝመትና ስፋት የሚበልጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
አዲሱ መርከብ ምንም እንኳን አዶራ ማጂክ ከተማ ከተሰኘችው የመጀመሪያዋ መርከብ መጠኑ ከፍ ያለ ቢሆንም፣ አጠቃላይ የግንባታው ሰዓት ከመጀመሪያው በ20 በመቶ እንደሚቀንስ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመርከብ አምራች ገልጿል።
 
መርከቡን የማስዋብ ስራ ሰኞ ዕለት መጀመሩን የገለፀው ኩባንያው፤ የዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ምቹ ሂደት የመርከቡን አጠቃላይ የግንባታ እና የማጓጓዣ መርሃ ግብር ለማረጋገጥ መሰረት ይጥላል ማለቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
 
አዶራ ማጂክ ከተማ የተሰኘችው የመጀመሪያዋ መርከብም ለሰባት ቀን እና ለስድስት ሌሊት ከ1 ሺህ 800 ኪሎ ሜትር በላይ የባህር ላይ ጉዞ ካከናወነ በኋላ በፈረንጆቹ ጥር ወር ላይ የመጀመሪያ የንግድ ጉዞውን ማጠናቀቁም ተመላክቷል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.