Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ1 ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 798 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 169 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው እድሜያቸው ከ1 እስከ 78 አመት የእድሜ ክልል የሚገኝ ሲሆን፥ 111 ወንድ እና 58 ሴቶች ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 168ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ አንደኛው ደግሞ የአሜሪካ ዜጋ ነው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 138 በአዲስ አበባ፣ 4 ትግራይ ክልል፣ 4 ደቡብ ክልል፣ 11 ኦሮሚያ ክልል፣ 6 አማራ ክልል፣ 1 ሐረሪ ክልል እንዲሁም 5 ከሶማሌ ክልል መሆናቸው ተገልጿል።

ባለፉት 24 ሰአታት የ35 አመት ሴት በቫይረሱ ሳቢያ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን፥ ይህም በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎችን ቁጥር 19 አድርሶታል።

በቫይረሱ ህይወቷ ያለፈው ግለሰብ ለአስከሬን በሆስፒታል በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባት ተረጋግጧል።

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት 12 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ፥ ከዚህ ውስጥ 10 ከአማራ ክልል እንዲሁም 2ቱ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 262 ደርሷል፤ 18 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.