Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የኢትዮጵያን ገፅታ ከፍ ባደረገ መልኩ መካሄዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት 37ኛው መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የኢትዮጵያን ክብርና ገፅታ ከፍ ባደረገ መልኩ ማስተናገድ መቻሉ ተገለጸ፡፡

የአፍሪካ ሕብረት 37ኛው መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባን ያሰናዳው ብሔራዊ ኮሚቴ ዛሬ ግምገማ አካሂዷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታና የብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በግምገማው ወቅት÷ የዘንድሮው ጉባዔ የኢትዮጵያን ክብርና ገፅታ ከፍ ባደረገ መልኩ ማስተናገድ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ስኬቱ ብሔራዊ ኮሚቴው ከሶስት ወራት በላይ ያደረገው ሰፊ ዝግጅት ውጤት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በውጤታማነት በመወጣታቸው ጉባዔው የሀገራችንን ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ ጉባዔዎችን የማስተናገድ ተሞክሮና አቅም ባስመሰከረ መልኩ ተካሂዶ እንዲጠናቀቅ አድርጓል ብለዋል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን የሕብረቱ ጉባዔ ከዘንድሮው የላቀ ለማድረግም ከወዲሁ ዝግጅት እንዲጀመር የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.