Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓድዋ ድልን አስመልክቶ ሀገር አቀፍ ውይይት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ‘‘ዓድዋ የህብረ ብሄራዊነት ድምቀት የአንድነት ውጤት’’ በሚል ሀገር አቀፍ ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ 128ኛውን የዓድዋ ድል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ÷ የተለያዩ ፅሁፎችም ቀርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ዓድዋ የዛሬ 128 ዓመት የተገኘ ድል ብቻ ሳይሆን ለዛሬው ትውልድና ለወደፊቱ ትውልድ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

የነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ እንድትሆን ልጆቿ ከታሪክና ከጀግንነት እንዲማሩ በማሰብ ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት እየሰራ እንደሚገኝም አመላተዋል፡፡

ለሀገር ትርጉም የሚሰጡ ውይይቶችን በማድረግም መሰል ዝግጅቶችን እንደ ባህል መትከል እንፈልጋለንም ነው ያሉት፡፡

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ (ፕ/ር) እናጄነራል ዓለምሸት ደገፌ ጥናታዊ ፅሁፎችን ያቀርባሉ።

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.