Fana: At a Speed of Life!

የሁለት ውሃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ መጽሐፍ ምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ ዋልታ እና የሁለት ውሃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ መጽሐፍ ምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እና በአዲስ ዋልታ በጋራ የተዘጋጀው የሁለት ውሃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ መጽሐፍ ምረቃ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው ፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ ÷ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሃብት በሚገባት ልክ ገና አልተጠቀመችበትም ብለዋል፡፡

ዛሬ የምንመርቀው ” የሁለት ውሃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ “መጽሐፍ አላማው ታሪክን መርምሮ ለነባራዊ ሁነቶቻችን መፍትሄ መስጠት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሃመድ ሀሰን በበኩላቸው ÷ትውልዱ ስለሁለቱ ውሃዎች እንዲያውቅ ፣እንዲማርና እንዲመራመር ስትራቴጂካዊ መንገዶችን ማወቅ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ይህንን ማድረግ ስንችልም የራሳችንን ዓድዋ መስራት እንችላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.