Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 658 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን አስመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በደብረብርሀን እና በአሰላ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 658 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ አስመርቋል።

ለሁለት ዓመታት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ተመራቂዎቹ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሰለጠኑ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡

የመምህራኑ ስልጠና ከተማዋ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ እንድትሆን የተሰነቀውውን ራዕይ ለማሳካት ትልቅ ሚና ያለው የትውልድ ግንባታችን አካል ነው ሲሉም አክለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.