Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ እስከአሁን 1ሺህ343 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እስከአሁን 1ሺህ343 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 169 ሰዎች ውስጥ 138 ሰዎች ከአዲስ አበባ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።

በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 138 ሰዎች መካከል 24 ሰዎች የካ ክፍለ ከተማ ፥ 23 ሰዎች ደግሞ ቦሌ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ።

እንዲሁም አዲስ ከተማ 20 ፣ ጉለሌ 19ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይም እስከአሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 375 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በልደታ 188 እንዲሁም በጉለሌ ክፍለ ከተማ 176ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.