Fana: At a Speed of Life!

ፖል ፖግባ ለ4 ዓመታት ከእግር ኳስ ጨዋታ ታገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖል ፖግባ ከአበረታች ንጥረ ነገር (ዶፒንግ) ጋር በተያያዘ ለአራት ዓመታት ከእግር ኳስ ጨዋታ ታግዷል፡፡
 
ፈረንሳዊው አማካይ አበረታች ንጥረ ነገር መውሰዱ በመረጋገጡ ነው ለ4 ዓመታት ከየትኛውም ዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጨዋታ የታገደው፡፡
 
በዚህም ፖል ፖግባ እስከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ በማንኛውም የፊፋ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ እንደማይሳተፍ ተመላክቷል፡፡

ፖግባ በጣሊያን ብሄራዊ ጸረ- አበረታች ቅመሞች ቡድን ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ምርመራ ሲደረግበት መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡

በተደረገው ምርመራም የ30 ዓመቱ አማካይ አበረታች ንጥረ ነገር (ዶፒንግ) መጠቀሙ ተረጋግጧል ።

ፖግባ ከቱሪኑ ክለብ ጁቬንቱስ ጋር የሁለት ዓመት ቀሪ ኮንትራት የሚቀረው ሲሆን÷ ቅጣቱን ተከትሎ ድጋሚ በክለቡ መለያ የመታየቱ ጉዳይ አጠራጣሪ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.