Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በናይሮቢ ቆይታቸው ፥ የኬንያ መከላከያ ሃይል ዋና መስሪያ ቤትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በዚህም ከኬንያ አቻቸው ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ ጋር የሁለቱን ሀገራት ትስስር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ወታደራዊ መሪዎቹ በሀገራቱ የጋራ ፍላጎቶችና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡

የቀጣናውን ደህንነት ማስጠበቅ፣ የመከላከያ ትብብር እና የጋራ ስልጠና ልምምዶችን ማሳደግ በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥና ቀጣናዊ ልማትን በማስፋፋት ትብብራቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፥ የኬንያ መከላከያ ሠራዊት ላደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና መስተንግዶ አመስግነዋል፡፡

ከጎረቤት ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነትን ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ፥ በቀጣናው ሰላምና ብልጽግናን በጋራ የመፍጠር ራዕይ ሊኖር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የሀገራቱን ትብብር በማጠናከር እና ተግዳሮቶችን በጋራ በመፍታት እድሎችን መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

#Ethiopia #Kenya

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.