Fana: At a Speed of Life!

የካፒታል ገበያውን በተዓማኒነት ማንቀሳቀስ የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ መሠረተ ልማቶችን ለማጠናከር፣ ግልጽነትን ለማጎልበትና የቴክኖሎጂ አቅምን ለማዳበር የሚያስችሉ ሁለት ስምምነቶችን ተፈራርሟል፡፡

የመጀመሪያው ስምምነት ‘’የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዓማኒነት ግብረ ኃይል የትብብር እና ቅንጅት የመግባቢያ ሰምምነት ቁ. 01/2016’’ተብሎ እንደሚጠራ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መካከል የተደረግ ነው፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ሕጋዊና ከወንጀል ድርጊቶች የጸዳ ለማድረግ፣ በተቋማቱ መካከል ቋሚና ቀልጣፋ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ የሕግ ማስከበር ስርዓት በመፍጠር የካፒታል ገበያውን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

2ኛው ስምምነት ደግሞ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተደረገ ስምምነት ሲሆን÷ ስምምነቱ በባለስልጣኑ፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መካከል ነው የተደረገው።

ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ያካተተው ስምምነቱ የባለሥልጣኑን የገበያ መቆጣጠር እና የኢንቨስተሮችን ደህንነት የመጠበቅ አቅሙን ማሳደግ እንደሚያስችል የባለሥልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ባለሥልጣኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በንቃት ለመከታተል እና ለመቅረፍ እንዲሁም አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፉን ለማሳደግ ዓላማ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.