Fana: At a Speed of Life!

የ6ኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫን ለማካሄድ የምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ይፋ መሆኑን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም በአራት ክልሎች ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ እንደሚካሄድ ነው ቦርዱ ያስታወቀው፡፡

ቀሪና የድጋሜ ምርጫው የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በተለያየ ምክንያት ባልተከናወነባቸው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምርጫውም በ29 የምርጫ ክልሎች፣ በ1 ሺህ 146 ምርጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በ34 የተፈናቃይ ምርጫ ጣቢያዎች እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡

ምርጫው የሚካሔደው ለዘጠኝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች እና ለ26 የክልል ምክርቤት መቀመጫዎች መሆኑን የቦርዱ ሠብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ አስታውቀዋል፡፡

በውብርስት ተሠማ እና ሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.